Get Mystery Box with random crypto!

የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጣይብ ኤርዶኻን ለኢትዮጵያ መንግሥት ምስጋና አቀረቡ..... የቱርክ | Ahmed Habib Alzarkawi

የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጣይብ ኤርዶኻን ለኢትዮጵያ መንግሥት ምስጋና አቀረቡ.....

የቱርክ ፕሬዚዳንት ረጀብ ጣይብ ኤርዶኻን የኢትዮጵያ መንግሥት በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው የርዕደ-መሬት አደጋ ወቅት ላደረገው አፋጣኝ የነፍስ አድን ድጋፍ እና ትብብር ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

ፕሬዚዳንቱ በቱርክ ለኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሐመድ እና ለኢትዮጵያ የነፍስ አድን ቡድን መሪ ሌ/ጄኔራል ደስታ አቢቼ የሜዳሊያ እና የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክተዋል።

ፕሬዚዳንት ረጀብ ጣይብ ኤርዶኻን በርዕደ-መሬት አደጋ ወቅት ድጋፍ ላደረጉ ሌሎች አገራትም የሜዳሊያ እና የምስጋና ምስክር ወረቀት ማበርከታቸውን በቱርክ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ገልጿል።