Get Mystery Box with random crypto!

ዘመናዊና ዘመን ተሻጋሪነት! በዛሬው እለት ለከተማችን አዲስ አበባ 3 ቢሊዮን ብር ገደማ ወጪ | Adanech abiebie

ዘመናዊና ዘመን ተሻጋሪነት!

በዛሬው እለት ለከተማችን አዲስ አበባ 3 ቢሊዮን ብር ገደማ ወጪ የሚደረግባቸው በአጠቃላይ ከ10 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው የመንገድ ፕሮጀክቶችን ለማስጀመር ከሶስት ተቋራጮች ጋር የፊርማ ስነስርዓት አከናውነናል፡፡

1. የመጀመርያው ከአፍሪካ ጎዳና - ኤድናሞል አደባባይ - 22 ማዞሪያ - እንግሊዝ ኢምባሲ የሚዘልቀው እጅግ ዘመናዊ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ለከተማዋ የመጀመሪያ የሆነውን Intelligent Transport System (ITS) ያካተተና የትራፊክ ፍሰትና ቁጥጥር ስርዓቱን ለማዘመን በከፍተኛ ደረጃ የሚያግዝ ፕሮጀክት ነው፡፡ ይህ ፕሮጀክት ከአለም ባንክ ባገኘነው ድጋፍ የሚከናወን ነው፡፡

2. ሁለተኛው የአየር ጤና - ወለቴ ሱቅ - ዓለም ገና አደባባይ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ነው፡፡

3. የመጨረሻው የአቃቂ ድልድይ ግንባታ ፕሮጀክት ነው፡፡
መላው የከተማችን ነዋሪዎች እነዚህ ፕሮጀክቶች የአዲስ አበባን ሁለንተናዊ እድገትና ገፅታ በእጅጉ የሚቀይሩ በመሆኑ፣ ለፕሮጀክቶቹ ስኬት እንደሁልጊዜውም ያልተቆጠበ ድጋፋችሁንና ከወሰን ማስከበር ስራው ጀምሮ አስፈላጊውን ሁሉ ትብብር እንድታደርጉ በዚህ አጋጣሚ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!



@adanechabiebie