Get Mystery Box with random crypto!

አቶ መለሰ ዓለሙ በአራዳ ክፍለ ከተማ በልዩ ሁኔታ በ90 ቀናት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረ | የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

አቶ መለሰ ዓለሙ በአራዳ ክፍለ ከተማ በልዩ ሁኔታ በ90 ቀናት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው ተመለከቱ

የብልፅግና ፓርቲ አዲስ አበባ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ በአራዳ ክፍለ ከተማ በልዩ ሁኔታ "አራዳን እንደገና" በሚል በ90 ቀናት እየተከናወኑ ያሉ ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን ያሉበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

"አራዳ እንደገና" በሚል ከተያዙ የልማት ፕሮጀክቶች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት በእቅድ መሰረት ተጠናቀው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል እየተደረገ ያለ የአመራር ድጋፍና ክትትል በመስክ ተገኝተው ጎብኝት አከናውነዋል።

የአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ተያይዘው የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ የተቋማትን ምላሽ የመስጠት አቅም ለመፍጠር የተጀመሩ ስራዎችም የጉብኝቱ አካል ነበሩ፤ በወረዳ 06 በሚገኘው ጃንሜዳ ጤና ጣቢያ እየተከናወነ ያለውን የአገልግሎት አሰጣት የማሻሻል ስራ የተመለከቱት አቶ መለሰ የጤና ተቋሙን በ90 ቀን በሰው ተኮር ስራዎች ተቋማትን ሞዴል ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች በተቋሙ ያለቱን ቦታዎች በአግባቡ በመጠቀም እና አገልግሎትን በማዘመን የተገልጋይ እንግልት የሚያስቀር ወጪና ብክነት ቀናሽ እንዲሁም የቁጥጥር ስራ የሚያቀላጥፍ ብሎም ሌብነትን የሚገታ ወረቀት አልባ አገልግሎት ጅምር አበረታች እንደሆነ ተመልክተዋል።

በጤና ተቋሙ ለሚመጡ መስማት ለተሳናቸው ተገልጋዮች አገልግሎት መስጠት እንዲያስችል የምልክት ቋንቋ ስልጠና ለተቋሙ ሰራተኞች እየተሰጠ መሆኑን የተመለከቱት አቶ መለሰ ይህ አይነት ተግባር አካል ጉዳተኞችን ለማገልገል ያለውን ተነሳሽነት የሚያመለክት በመሆኑ ይህ ተግባር በሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በተሞክሮ መልክ ለመስፋት የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።

በክፍለ ከተማው ወቅታዊ የፀጥታ ስራ መልካም አፈፃፀም የታየበት ሲሆ በ90 ቀን የሚከናወኑ ሰው ተኮር የልማት ተግባራት በተያዘላቸው ጊዜ እና በፍጥነት ለማጠናቀቅ አመራሩ የሠላም የልማትና የመልካም አስተዳር ስራዎች ጎን ለጎን አስተሳስሮ የመስራት ልምዱን የበለጠ ማጠናከር እንደሚገባው አቶ መለሰ አሳስበዋል።


የፌስ ቡክ ግሩኘ https://facebook.com/groups/1214264802267291/