Get Mystery Box with random crypto!

ብልፅግና ፓርቲ በትውልድ ቅብብሎሽ ሁለንተናዊ ብልፅግናን እዉን የማድረግ ራዕይ ሰንቆ የተነሳ ፓርቲ | የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

ብልፅግና ፓርቲ በትውልድ ቅብብሎሽ ሁለንተናዊ ብልፅግናን እዉን የማድረግ ራዕይ ሰንቆ የተነሳ ፓርቲ ነው።

ብልፅግናን በማረጋገጥ ሂደት ሠላም መሠረታዊ አስፈላጊ እሴት ነው።
የብልፅግናው ጉዞ አልጋ በአልጋ እንደማይሆን የሚጠበቅ ቢሆንም የጉዞውን ሂደት የሚያደናቅፉ፣ የጉዞዉን ፍጥነት የሚገቱ የሠላምና የደህንነት ስጋቶችን ምንጫቸዉን በተቻለ መጠን ማድረቅ አስፈላጊ ነው።

የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግናን የማረጋገጡ ራዕይ እዉን እንዲሆን ራዕይው የአብዛኛው ህብረተሰብ የጋራ ራዕይ እንዲሆን፣ አንፃራዊ የሆነ የዓላማና የተግባር መሰናሰልንና አረዳድ መፍጠር ይጠይቃል።

በዓላማና በተግባር የተጣመረ የቁጭት መንፈስ በመፍጠር ፀጋዎቻችንን በማልማት ዘላቂና ተከታታይ እድገት ብቻ ሳይሆን ብልፅግናን ለማረጋገጥ የተጀመረውን ጥረት ዘላቂ ለማድረግ ሠላም መሠረታዊ ነዉ። የፖለቲካ ስብራቶቻችንን በማረም የወንድማማችነት እና የእህትማማችነት እሴቶችን እና ትርክቶችን ማጎልበትም ለዘላቂ ሰላም ወሳኝ ነው።

በተለይም አካታች ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ የልዩነት ሀሳቦችን በአንፃራዊነት አቀራርቦ የይቅርታና የፍቅር ድልድይ በመዘርጋት፣ ዘላቂ ሠላምን ማረጋገጥ የሚያስችል አይነተኛ መሣሪያ መሆኑን የተለያዩ ሀገራት ልምድ ያሳያል።

የአካታች ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ እና ዉጤቱ የተሳካ እንዲሆን ማድረግ ማለት ጠንካራ ዲሞክራሲን እና ዘላቂ ሠላምን ኢትዮጵያ ውስጥ ማረጋገጥ ማለት ነዉ።

ሠላም በጋራ ጥረት የሚሳካ መሠረታዊ ጉዳይ በመሆኑ የጉዳያችንን ማዕከል የኢትዮጵያ ሠላም፣ ልማትና ዲሞክራሲ እንዲሆን በማድረግ፣ አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ሰላም መሠረታዊ በመሆኑ ለዘላቂ ሠላም የየበኩላችንን ማበርከት አለብን።

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira