Get Mystery Box with random crypto!

አሸባሪው ህወሃት ህጻናትን በጦርነት ያለማሳተፍ የሚለውን መርህ በመጣስ የጦር ወንጀል እየፈጸመ መሆ | የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

አሸባሪው ህወሃት ህጻናትን በጦርነት ያለማሳተፍ የሚለውን መርህ በመጣስ የጦር ወንጀል እየፈጸመ መሆኑ ዳግም ይፋ እየወጣ ነው

አሸባሪው ህወሃት ህጻናትን በጦርነት ያለማሳተፍ የሚለውን የፓሪስ መርህ በመጣስ የጦር ወንጀል እየፈጸመ መሆኑ ዳግም ይፋ እየወጣ ነው።

የቡድኑን እንቅስቃሴ የሚያሳዩ ምስሎች እንዳሳዩት እድሜያቸው ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ያልደረሱ ታዳጊዎች በጦርነት እየተሳተፉ እንደሆነ በግልጽ ታይቷል።

በዚህም ህጻናት በጦርነት እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፍ ወታደራዊና ሌሎች ተዛማጅ አገልግሎቶችን መስጠት እንደማይችሉ የሚገልጸውን የፓሪስ መርህን በመጣስ ህጻናትን በገፍ ለጦርነት በማሰለፍ የጥይት ማብረጃ እያደረጋቸው ይገኛል።

በመሆኑም ይህ ከመርህ የወጣ የአሸባሪ ቡድኑ ድርጊት የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ ሊያወግዘው እንደሚገባ እየተጠቆመ ይገኛል።

ከዚህ ቀደም አሸባሪው ህወሃት በአፋርና አማራ ክልሎች ወረራ በፈጸመበት ወቅት ህጻናትን በሃሺሽ አስክሮ በማስገባት በተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ህጻናትን ማስጨረሱ ይታወሳል።

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira
የፌስ ቡክ ግሩኘ https://facebook.com/groups/1214264802267291/