Get Mystery Box with random crypto!

በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ ከብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የተሰ | የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር፣ ከብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

የተከበራችሁ የሀገራችን ሕዝቦች፣
ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤት ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ሀገራዊ የደኅንነት ሁኔታ የገመገመ ሲሆን፣ በቀደሙት ወራት ተለይተው የነበሩ ሀገራዊ ሥጋቶችን መሠረት በማድረግ የተከናወኑ ተግባራትንና ያጋጠሙ ውስንነቶችን ለግምገማው መነሻ አድርጓል። የደኅንነት ምክር ቤቱ ሰኔ 1 ባካሄደው ስብሰባው ወቅት በአስቸኳይ ለማከናወን ተወስነው ከነበሩ ተግባራት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡-
1. አሸባሪና የታጠቁ ቡድኖችን በአመራራቸው ላይ ትኩረት በማድረግ ለመደምሰስ፣
2. ለጠላት ዐቅም የሚሆነው ከዳተኛ የጸጥታ ኃይል ስለሆነ፣ የዚህን ምክንያት፣ መነሻና ዋና ዋና ተዋንያን ለመለየት፣
3. ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን እያወያዩ፣ በዓላማና በተግባር ላይ እየተግባቡ፣ የጋራ ተግባርን ለማቀናጀትና ግጭቶችን ትርምስ
አልባ ወደሚሆኑበት መጠን ለመቀነስ፣
4. የሥጋት መነሻና የሥጋት ተዋንያን የሆኑ አካላትን ለማወያየትና ራሳቸውን ከሥጋት መነሻነትና ከሥጋት ተዋናይነት እንዲነጥሉ
ለማድረግ፣
5. የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደቀድሞ አካባቢያቸው በመመለስ ለማቋቋም፤ የፈረሱ የመንግሥት መዋቅሮችን መልሶ ለማደራጀትና ሥራ
እንዲጀምሩ ለማድረግ፣
6. ኮንትሮባንድ፣ የኢኮኖሚ አሻጥር፣ ግድያ፣ ዝርፊያ፣ ኢመደበኛ አደረጃጀት፣ ወዘተ. ዓይነት ሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎችን ከሥራቸው
ነቅሎ ለማስቆም፣
7. የፍትሕና የጸጥታ ተቋማትን ለማስተካከል አቅጣጫዎች ተቀምጠው ነበር።
እነዚህን አቅጣጫዎች መሠረት በማድረግ የተከናወኑ ተግባራትን የተመለከተው የደኅንነት ምክር ቤቱ እጅግ ወሳኝ፣ ችግር ፈቺ፣ ተግዳሮቶችን የሚቀንሱ፣ ሰላምና ጸጥታን ለማስፈንና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎቻችንን ለማሳለጥ የሚጠቅሙ ተግባራት በክልሎችና በፌዴራል ደረጃ እየተከናወኑ መሆኑን አድንቋል።
በኦሮሚያ ክልል ሸኔን ለመደምሰስ የሚያስችሉ የሸዋ፣ የወለጋ፣ የጉጂ ኮማንድ ፖስቶች የተደራጁ ሲሆን፤ መከላከያ፣ የክልሉ አመራርና የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች በጋራ የተቀናጀ ሥምሪት እያካሄዱ ይገኛሉ። በዚህም 3180 የሸኔ ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆን እጃቸውን ላለመስጠት አሻፈረኝ ያሉት ተደምስሰዋል። በተጨማሪም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የአባ ቶርቤ፣ የአልሸባብና የጁንታው ሴሎችና ተባባሪዎች ተይዘዋል። በኦፕሬሽኑ በርካታ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሣሪያዎች፣ ተተኳሾች፣ ተሽከርካሪዎች፣ ገንዘብና ልዩ ልዩ ንብረቶች ከጠላት ተማርከዋል። በጠላት ተይዘውና ፈርሰው ከነበሩ 1,739 ቀበሌዎች መካከል 1,255 ያህሉ እንደገና ተደራጅተዋል። 252,129 የቤተሰብ አባላትን የያዙ 47,558 አባዎራዎች ወደ ቀድሞ ቀያቸው ተመልሰዋል።
በተመሳሳይ በአማራ ክልል ሕግን ለማስከበር በተወሰደው የተቀናጀ የጸጥታ ኃይሎች፣ የአመራሩና የሕዝቡ ሥምሪት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተጠርጣሪዎች በሕግ ጥላ ሥር ውለዋል። ከእነዚህ መካከል ገሚሱ የጸጥታ ኃይሎችን በመክዳት ለሕገ ወጥ ታጣቂዎች ዐቅም ሲፈጥሩ የቆዩ ሲሆኑ፣ የተቀሩት በልዩ ልዩ ወንጀሎች ሲፈለጉ የከረሙ ናቸው። ከወያኔ ጋር ወግነው በክልሉ የሚኖሩ ሕዝቦችን እርስ በእርስ ለማጋጨት የሚሰሩ ታጣቂዎች ላይ ርምጃ የተወሰደ ሲሆን፣ ጠላት ተጨማሪ ሰው የማያገኙበት ደረጃ ላይ ለማድረስ እየተሠራ ነው። ከቅማንት ሕዝብ ጋር በተገናኘ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት እንዲሁም በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ተከስቶ የነበረውን ጸጥታ ችግር እንዳይባባስ ለማድረግ የውይይት መድረኮች ተዘጋጅተው የተሻለ መግባባት ተፈጥሯል፡፡
በአጠቃላይ በክልሉ እስካሁን ድረስ ከ6.6 ሚልዮን በላይ ሕዝብ የተሳተፈባቸው የውይይት መድረኮች የተካሄዱ ሲሆን፣ በ633 አመራሮችና ባለሞያዎች ላይም ከመጀመሪያ ማስጠንቀቂያ ጀምሮ በሕግ ቁጥጥር ሥር እስከማዋል የደረሰ ርምጃ ተወስዷል።
በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብን ጸጥታና ደኅንነት ከማረጋገጥ አንጻር መልካም ተግባራት መከናወናቸውን የደኅንነት ምክር ቤቱ በግምገማው ተረድቷል። ከ497 በላይ የጁንታው፣ የሸኔ፣ የአልሸባብና ሌሎች አክራሪ ቡድኖች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። ከእነርሱም ጋር የጸጥታ ኃይሎች አልባሳት፣ ሐሰተኛ መታወቂያዎች፣ ማኅተሞች፣ ለሽብር ተግባር የተዘጋጁ ሰነዶች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፣ የጦር መሣሪያዎች፣ ተሸከርካሪዎች፣ ለአሸባሪዎች ሊላኩ የነበሩ ተንቀሳቃሽ ስልኮች እና የባንክ ደብተሮች አብረው በቁጥጥር ሥር ውለዋል። የተደራጁ ወንጀሎችን ሲመሩ የነበሩ 314 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉ ሲሆን፣ 75 ከተማና የፌዴራል መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በሙስና ተጠርጥረው ተይዘዋል። በመሬት ወረራ የተወሰዱ መሬቶችን ማስመለስ እና ሕገወጥ ግንባታ የተፈጸመባቸው በጥቅሉ በ1596 ቦታዎች ላይ እርምጃ መውሰድ ተችሏል። በአዲስ አበባ የተሠራው ሥራ ውጤት ማምጣቱን የደኅንነት ምክር ቤቱ ያረጋገጠ ሲሆን÷ የፍትሕ አካላትን ከማጥራት አንጻር በበቂ ሁኔታ እንዳልተሠራ ገምግሟል፡፡ በተጨማሪም በከተማዋ የሚደረጉ የሕዝብ ውይይቶች በበቂ መተማመን የፈጠሩ አለመሆናቸውን፤ በሽብር እንቅስቃሴ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ አካላትን ከዚህ በላይ ማጋለጥና መቆጣጠር እንደሚገባ፤ ሙስናና የኢኮኖሚ አሻጥርን መልክ ለማስያዝ በሙሉ ኃይልና በቁርጠኝነት መሥራት እንደሚያስፈልግ ምክር ቤቱ አሥምሮባቸዋል።
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ያለው የሥጋት ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ፣ ሰላምና ደኅንነት ይበልጥ እየተረጋገጠ መምጣቱን ብሔራዊ የደኅንነት ምክር ቤቱ ተመልክቷል። በክልሉ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሕገ ወጥ ታጣቂዎች የተደመሰሱ ሲሆን፣ 1,826 የሚደርሱ ታጣቂዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል። 749 ልዩ ልዩ የጦር መሣሪያዎች እና 5,639 ተተኳሾች ከጠላት የተማረኩ ሲሆን፣ 9 ጀልባዎችና 65 የጠላት ካምፖችም ወድመዋል። እጃቸውን በሰላም የሰጡ ሕገወጥ ታጣቂዎችን ወደ መደበኛ ሕይወት የማስገባት እንዲሁም፤ በከማሺና በመተከል ዞኖች 171,485 ተፈናቃዮችን የማቋቋም ሥራ ተሠርቷል። ከጠላት ነጻ ከወጡ 180 ቀበሌዎች
መካከል በ169ኙ የመንግሥት መዋቅር መልሶ ተደራጅቷል። በክልሉ አንጻራዊ ሰላም መስፈኑን፣ የሽፍታ ቡድኖች ዐቅም መዳከሙን፣ ተፈናቃዮችን መልሶ የማቋቋም ተግባር እየተሻሻለ መሄዱን፣ የደኅንነት ምክር ቤቱ በአዎንታዊነት የገመገመ ሲሆን፣ በቀጣይ ሊከናወኑ የሚገቡ ያልተጠናቀቁ ተግባራት መኖራቸውንም አይቷል። ከእነዚህም መካከል ከሸኔና ከጁንታው ጋር እየተቀናጀ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሰውን የሽፍታ ቡድን ሙሉ በሙሉ የመደምሰስ፤ የመንግሥትን መዋቅር መልሶ ወደ ሥራ የማስገባት፤ በሰላም የገቡትን ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ የማቋቋም ተግባራት ይገኙበታል። የክልሉ አመራሮች፣ የጸጥታ ኃይሎችና ሕዝቡ እነዚህን ተግባራት በቀሪ ጊዜያት እንደሚያከናውኗቸው ምክር ቤቱ የጸና እምነቱ መሆኑን አመልክቷል።
በደቡብ ክልል እየተከናወነ የሚገኘው ሰላምንና ደኅንነትን የማረጋገጥ ሥራ ካለፉት የተሻለ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የደኅንነት ምክር ቤቱ ገምግሟል። ከብሔረሰቦች የሚነሡ የአደረጃጀት ጥያቄዎችን የመለየትና ለሀገርና ለሕዝብ ዘላቂ ጥቅም በሚያስገኝ መንገድ ለመፍታት እየተሠራ ነው። ጥያቄዎችን ለመፍታት የሚያስችል ሁኔታ በመፈጠሩ በኢመደበኛነት ተደራጅቶ ጫና የሚፈጥር ኃይል ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እየተመሰለ ነው። በአዋሳኝ አካባቢዎች የሚታየውን የሸኔ እንቅስቃሴ ከአጎራባች ክልሎች ጋር ተቀናጅቶ የማስወገድ፤ ከክልል መደራጀት ጋር የሚነሡ ጥያቄዎችንና