Get Mystery Box with random crypto!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይ | የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 10ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

ምክር ቤቱ በቀዳሚነት የተወያየው የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣንን አደረጃጀት፣ ስልጣንና ተግባራትን ለመወሰን በቀረበው ደንብ ላይ ሲሆን÷ የፌዴራል መንግስት የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 የነዳጅና ኢነርጂ ጉዳዮችን የሚመራ ተቋም በአዲስ መልከ ያቋቋመ መሆኑን ተከትሎ ባለስልጣኑ ሴክተሩን በብቃት መምራት የሚያስችል ስልጣንና ተግባር እንዲኖረው የሚያስችል ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምከር ቤት ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ በሰፊው ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣት ቀን ጀምሮ በሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

በመቀጠል ምክር ቤቱ ውይይቱን ያደረገው የብሔራዊ የክፍያ ስርዓት አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡

ቀደም ሲል የነበረውን አዋጅ ማሻሻል ያስፈለገበት ዋነኛ ምክንያት አገራችን በጀመረችው አጠቃላይ አገራዊ የሪፎርም አጀንዳ ማዕቀፍ ውስጥ የክፍያ አገልግሎት ሰጪዎችን ተሳትፎ በማስፋት የክፍያ ስርዓቱን ውጤታማነት፣ አስተማማኝነትና ተወዳዳሪነት ለማጎልበት፣ ገበያው አበከሮ የሚፈልጋቸውንና በዘርፉ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረጉትን ለውጦች፣ ዕድገቶችና መሻሻሎች ታሳቢ ባደረገ መልኩ የክፍያ ስርዓታችንን ማዘመን ይቻል ዘንድ የማሻሻያ አዋጅ ተዘጋጅቶ ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ምክር ቤቱ በመቀጠል የተወያየው ከጣሊያን ሪTብሊክ መንግስት ለጤናው ዘርፍ ዘላቂ የልማት ግቦች ፕሮጀክት እንዲሁም ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ በተፈቀዱ ብድሮች ማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ነው፡፡

ከጣሊያን መንግሥት የተገኘው ብድር 10 ሚሊየን ዩሮ ሲሆን፥ ከዓለም አቀፉ የልማት ማህበር የተገኘው ብድር ደግሞ 400 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ነው፡፡

ምክር ቤቱም ብድሮቹ ከ 1 ፐርሰንት ያነሰ ወለድ የሚከፈልባቸው፣ እስከ 12 ዓመታት የሚደርስ የችሮታ ጊዜ ያላቸው እና በ38 ዓመታት ተከፍለው የሚጠናቀቁ መሆናቸውን፥ ይህም ከአገራችን የብድር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም መሆኑን በማረጋጥ ይጸድቁ ዘንድ ረቂቅ አዋጆቹን ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡

ምከር ቤቱ በመጨረሻ ውይይቱን ያደረገው የፌዴራል የገቢ ግብር ደንብን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ነው፡፡

በካፒታል እጥረት ምክንያት የስራ እንቅስቃሴያቸው የተዳከሙ ድርጅቶች ተጨማሪ ካፒታል ለማሰባሰብ ከሚሸጡት አዲስ አከሲዮን የሚ7ኝ ገቢን ከግብር ነጻ ማድረግ የሚኖረውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከግምት ውስጥ በማስባት እንደዚሁም በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር ቁጥር 979/2008 አንቀጽ 65 (2) ኢኮኖሚያዊ አስተዳደራዊ ወይም ማህበራዊ ምክንያቶች መኖራቸው ሲታመን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ድንብ በማውት አንድን ገቢ ከግብር ነፃ ሊያደርግ እንደሚችል በተደነገገው መሰረት ረቅቅ ደንብ ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በደንቡ ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በነጋሪት ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወበት ቀን ጀምሮ በስራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡