Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ ችላ በማለት ከሕግ ውጪ ነዳጅ | የጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ እውነተኛ ደጋፊዎች

የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ ችላ በማለት ከሕግ ውጪ ነዳጅ የጫኑ ስምንት የነዳጅ ቦቴዎችን መውረሱን አስታወቀ፡፡

ሆን ብለው የነዳጅ እጥረት እንዲከሰትና ከመንግስት የተሰጠውን መመሪያና ደንብ ችላ በማለት ከሕግ ውጪ ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ወደ ከተማ እንዳይገቡ ያደረጉ ስምንት የነዳጅ ካምፓኒዎች ቦቴዎች በዛሬው እለት በፀጥታ ሀይሎችና በህብረተሰቡ ጥቆማ ተወርሰዋል፡፡ የተወረሰው ነዳጅም በነዳጅ ማደያዎች በኩል እንዲከፋፈል ማድረጉን ቢሮው አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መስፍን አሰፋ ÷ ሕግ አክብረው በማይሰሩና በትክክል ስራቸውን በማይወጡ የነዳጅ ካምፓኒዎች ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የቴሌግራም ቻናል https://t.me/abdisira